ፈርዖን ቀለበቱን ከእጁ አወለቀ፤ በዮሴፍም እጅ አደረገው፤ የነጭ ሐር ልብስንም አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ዝርግፍን አደረገለት፤
መዝሙር 73:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁ በመጥረቢያና በመዶሻ ሰበሩአት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ትዕቢት የዐንገት ጌጣቸው ነው፤ ዐመፅንም እንደ ልብስ ተጐናጽፈዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ትዕቢት የአንገት ሐብላቸው፥ ዓመጽ መጐናጸፊያቸው ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ትዕቢትን እንደ ድሪ አጥልቀዋል፤ ዐመፅንም እንደ ልብስ ለብሰዋል። |
ፈርዖን ቀለበቱን ከእጁ አወለቀ፤ በዮሴፍም እጅ አደረገው፤ የነጭ ሐር ልብስንም አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ዝርግፍን አደረገለት፤
ክፉን ከሚያደርጉ ወገን ፈጥኖ ክርክርን የሚያደርግ የለምና፤ ስለዚህ የሰው ልጆች ልብ በእነርሱ ክፉን ለመሥራት ጠነከረ።
“ሞአብ ከልጅነቷ ጀምራ ዐረፈች፤ በክብርዋም ቅምጥል ነበረች፤ ወይንዋም ከዕቃ ወደ ዕቃ አልተገላበጠም፤ ወደ ምርኮም አልሄደችም፤ ስለዚህ ቃናው በእርስዋ ውስጥ ቀርቶአል፤ መዓዛዋም አልተለወጠም።
እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት እንዲህ ይላል፥ በጥርሳቸው ሲነክሱ በሰላም ይሰብካሉ፥ በአፋቸው ግን አንዳች በማይሰጥ ሰው ላይ ሰልፍን ያስቡበታል።
ያዕቆብ በላ፤ ጠገበም፤ የተወደደውን ጥጋብ አቀናጣው፤ ሰባ፥ ወፈረ፥ ሰፋ፤ የፈጠረውንም እግዚአሔርን ተወ፤ ከሕይወቱ ከእግዚአብሔርም ራቀ።
እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።
የለመነውም የወርቅ ጕትቻ ሚዛኑ ከአምባሩ፥ ከድሪውም፥ የምድያምም ነገሥታት ከለበሱት ከቀዩ ቀሚስ፥ በግመሎቻቸውም አንገት ከነበሩት ሥሉሴዎች ሌላ ሺህ ሰባት መቶ ሰቅለ ወርቅ ነበረ።