ጠላት በቅዱሳንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁልጊዜ በትዕቢታቸው ላይ እጅህን አንሣ።
ክፉዎች ሲሳካላቸው አይቼ፣ በዐመፀኞች ቀንቼ ነበርና።
የክፉዎችን ሰላም አይቼ በዓመፀኞች ቀንቼ ነበርና።
ይህም የሆነው ትዕቢተኞችና ክፉዎች ሰዎች ሲበለጽጉ በማየቴ ቅናት አድሮብኝ ነው።
እግዚአብሔርን የሚያስቈጡትን ሰዎች፥ እርሱ የሚመረምራቸው አይደለምን?
ደስታዬን ተማምኛት ነበር፤ ነገር ግን ጠፋችብኝ፤ አግባብስ ወደ ኃጥኣን ትመለስ ዘንድ ነው።
ስለ ምን ኀጢኣተኞች በሕይወት ይኖራሉ? በባለጠግነትስ ስለ ምን ያረጃሉ?
በታመመም ጊዜ መዳንን ተስፋ አያደርግም። ነገር ግን እርሱ በሕማሙ ይሞታል።
እግዚአብሔር ጻድቁንና ኃጥኡን ይመረምራል፤ ዐመፃን የወደዳት ግን ነፍሱን ጠልቶአል።
አቤቱ፥ በመዓትህ አትቅሠፈኝ፥ በመቅሠፍትህም አትገሥጸኝ።
ነፍሴ ስድብን ጠግባለችና፥ ለሥጋዬም ድኅነትን አጣሁ።
ልብህ በኀጢአተኞች አይቅና፤ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር፤
ልጄ ሆይ፥ በክፉ ሰዎች አትቅና፥ ከእነርሱም ጋር መኖርን አትውደድ፤
ከክፉ ሰዎች ዘንድ ሽሙጥን ገንዘብ አታድርግ፥ በመንገዳቸውም አትቅና።
ጻድቅ በጽድቁ ሲጠፋ፥ ኃጥእም በክፋቱ ሲኖር፥ ይህን ሁሉ በከንቱ ዘመኔ አየሁ።
አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኀጢአተኞች መንገድ ስለ ምን ይቀናል? በደልንስ የሚያደርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላቸዋል?
አሁንም የሚታበዩትን ሰዎች ብፁዓን ብለን እንጠራቸዋለን፣ ክፉንም የሚሠሩ ጸንተዋል እግዚአብሔርንም ይፈታተናሉ፥ ያመልጣሉም ብላችኋል።
ወይስ መጽሐፍ “በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል፤” ያለው በከንቱ እንደ ተናገረ ይመስላችኋልን?