አቤቱ፥ ተነሥ፥ በቀሌንም ተበቀል፤ ሰነፎች ሁልጊዜ የተገዳደሩህን ዐስብ።
ደነዝና አላዋቂ ሆንሁ፤ በፊትህም እንደ እንስሳ ሆንሁ።
እኔ የተናቅሁ ነኝ አላወቅሁምም፥ በአንተ ዘንድም እንደ እንስሳ ሆንሁ።
ጌታ ሆይ! እኔ ለአንተ ከእንስሶች የማልሻል፥ ምንም የማይገባኝ አላዋቂ ነበርኩ።
ስለ ምንስ እንደ እንስሳ በፊትህ ዝም አልን?
እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑ፤ እርሱ አዘዘ፤ ተፈጠሩም።
የዱር አራዊት ሁሉ፥ የምድረ በዳ እንስሶችና ላሞች ሁሉ የእኔ ናቸውና።
እኔ ድሃና ምስኪን ነኝ፤ እግዚአብሔርም ይረዳኛል፤ ረዳቴ መጠጊያዬም አንተ ነህ፥ አቤቱ አምላኬ አትዘግይ።
እኔ በልቤ ስለ ሰው ልጆች ነገር፥ “እንደ እንስሳ መሆናቸውን ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል” አልሁ።
በሬ ገዢውን አህያም የጌታውን ጋጥ ዐወቀ፤ እስራኤል ግን አላወቁኝም፤ ሕዝቤም አላስተዋሉኝም።”