ወደ ኪዳንህም ተመልከት፥ የምድር የጨለማ ስፍራዎች በኃጥኣን ቤቶች ተሞልተዋልና።
ሰው ከሕልሙ ሲነቃ እንደሚሆነው፣ ጌታ ሆይ፤ አንተም በምትነሣበት ጊዜ፣ እንደ ቅዠት ከንቱ ታደርጋቸዋለህ።
ከሕልም እንደሚነቃ፥ አቤቱ፥ ስትነቃ መልካቸውን ትንቃለህ።
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ስትነሣ እነርሱ በማለዳ እንደሚረሳ ሕልም ይጠፋሉ።
እንደ ሕልም ይበርራል፤ እርሱም አይገኝም፤ ሲነጋም እንደማይታወቅ እንደ ሌሊት ራእይ ይሰደዳል።
መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድሁም፤ ሥጋህን አንጻልኝ፤ የሚቃጠለውንና ስለ ኀጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልወደድሁም።
አቤቱ፥ በመዓትህ ተነሥ፤ በጠላቶቼ ላይ ተነሣባቸው፤ አቤቱ፥ አምላኬ፥ ባዘዝኸው ሥርዐት ተነሥ።
ከሌሊት ግርማ፥ በመዓልት ከሚበርር ፍላጻ፥