ለድሆች ሕዝብህ በጽድቅ ፍረድ፥ የድሆችንም ልጆች አድናቸው። ትዕቢተኛውንም አዋርደው።
አምላኬ ሆይ፤ ከክፉ እጅ፣ ከግፈኛና ከጨካኝ መዳፍ አውጣኝ።
አምላኬ፥ ከክፉ እጅ፥ ከዓመፀኛና ከግፈኛም እጅ አድነኝ።
አምላኬ ሆይ! ከክፉ ኀይልና ርኅራኄ ከሌለው ዐመፀኛ እጅ አድነኝ።
ከሄዱም በኋላ እነርሱ ከጕድጓዱ ወጥተው ሄዱ፤ ለንጉሡም ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትንም፥ “አኪጦፌል በእናንተ ላይ እንዲህ መክሮአልና ተነሡ፤ ፈጥናችሁም ውኃውን ተሻገሩ” አሉት።
እግዚአብሔርም በሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ።
አቤቱ፥ በጆሮአችን ሰማን፥ አባቶቻችንም በዘመናቸው በቀድሞ ዘመን የሠራኸውን ሥራ ነገሩን።