አቤቱ፥ አንተን ታመንሁ፤ ለዘለዓለም አላፍርም።
አምላክ ሆይ፤ ታድነኝ ዘንድ ዘንበል በል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
ለመዘምራን አለቃ፥ ለመታሰቢያ፥ የዳዊት መዝሙር።
አምላክ ሆይ! አድነኝ! እግዚአብሔር ሆይ! ፈጥነህም እርዳኝ!
እጅህን ከአርያም ላክ፥ ከብዙ ውኃም አድነኝ፤ ከባዕድ ልጆችም እጅ፥
“በአንደበቴ እንዳልስት አፌን እጠብቃለሁ፤ ኃጥኣን በፊቴ በተቃወሙኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ” አልሁ፤
ድሃውን ከሚቀማው እጅ፥ ረዳት የሌለውንም ምስኪን ያድነዋልና።