የአሕዛብም ጉባኤ ይከብብሃል፤ ስለዚህም ወደ አርያም ተመለስ።
የሕዝቦች ጉባኤ ይክበብህ፤ አንተም ከላይ ሆነህ ግዛቸው፤
አቤቱ፥ በመዓትህ ተነሥ፥ በጠላቶቼ ላይ በቁጣ ተነሣባቸው፥ አቤቱ አምላኬ፥ ባዘዝኸው ትእዛዝ ንቃ።
ሕዝቦችን ሁሉ በዙሪያህ ሰብስብ፤ ከላይም ሆነህ ንገሥ።
ዕውቀትህ በእኔ ላይ ተደነቀች፤ በረታችብኝ፥ ወደ እርሷም ለመድረስ አልችልም።
አቤቱ፥ በጆሮአችን ሰማን፥ አባቶቻችንም በዘመናቸው በቀድሞ ዘመን የሠራኸውን ሥራ ነገሩን።
መቃብራቸው ለዘለዓለም ቤታቸው ነው፥ ማደሪያቸውም ለልጅ ልጅ ነው፤ በየሀገራቸውም ስማቸው ይጠራል።
ወዳጆችህም፥ እንዲድኑ በቀኝህ አድን፥ ስማኝም።
ይከራከራሉ፥ ዐመፃንም ይናገራሉ፤ ዐመፃንም የሚያደርጉ ሁሉ ይናገራሉ።
ለዘለዓለም በአርያም የሚኖር ስሙም ቅዱሰ ቅዱሳን የሆነ፥ በቅዱሳን አድሮ የሚኖር፥ ለተዋረዱት ትዕግሥትን የሚሰጥ፥ ልባቸውም ለተቀጠቀጠ ሕይወትን የሚሰጥ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ! በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”