መዝሙር 7:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚገድል መርዝንም አዘጋጀበት፤ ፍላጻዎቹንም የሚቃጠሉ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚገድሉ ጦር ዕቃዎቹን አሰናድቷል፤ የሚንበለበሉትን ፍላጻዎቹንም አዘጋጅቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለማይመለስ ግን ሰይፉን ይስላል፥ ቀስቱን ወጥሮአል አዘጋጅቷልም፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚገድሉ የጦር መሣሪያዎችን ያበጃል፤ እንደ እሳት የሚንበለበሉ ፍላጻዎችንም ያዘጋጃል። |
ዳሌጥ። ቀስቱን እንደ ተቃዋሚ ጠላት ገተረ፤ እንደ ባላጋራም ቀኝ እጁን አጸና፤ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን ለዐይኑ የሚያምረውን ሁሉ ገደለ፤ መዓቱንም እንደ እሳት አፈሰሰ።
ሰይፌን እንደ መብረቅ እስላታለሁ፤ እጄም ፍርድን ትይዛለች፤ ለሚጠሉኝም ፍዳቸውን እከፍላለሁ፤ ጠላቶችንም እበቀላለሁ።
ጌታ ኢየሱስ ከኀያላን መላእክቱ ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።
በታላቅ ድምፅም እየጮኹ “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” አሉ።