አቤቱ፥ እኔን ለማዳን ተመልከት፤ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።
አምላክ ሆይ፤ አድነኝ፤ ውሃ እስከ ዐንገቴ ደርሶብኛልና።
ለመዘምራን አለቃ፥ በመለከቶች፥ የዳዊት መዝሙር።
የውሃ ሙላት እስከ አንገቴ ስለ ደረሰ፤ አምላክ ሆይ! አድነኝ!
ብርሃኑም ጨለማ ሆነብህ፥ ተኝተህም ሳለህ ውኃው አሰጠመህ።
ቃላቸው ወደ ምድር ሁሉ ወጣ። ነገራቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ።
በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ፤
አምላካችን መጠጊያችንና ኀይላችን ነው፤ ባገኘን በታላቅ መከራም ጊዜ ረዳታችን ነው።
አምላኬ ሆይ፥ ልመናዬን ስማኝ፥ ጸሎቴንም አድምጠኝ።
ነፍሴን የሚሹአት ይፈሩ፥ ይጐስቍሉም፥ ክፉንም የሚመክሩብኝ ወደኋላቸው ይመለሱ፥ ይፈሩም።
በረዳታችን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፥ ለያዕቆብም አምላክ እልል በሉ።
ፍርዴን ለተስፋ ይቅርታዬንም ለትክክለኛ ሚዛን አደርጋለሁ፤ በከንቱና በሐሰት የሚታመኑ ከዐውሎ ነፋስ አያመልጡም።
በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ ወንዞችም አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።
በራሴ ላይ ውኃ ተከነበለ፤ እኔም፥ “ጠፋሁ” ብዬ ነበር።
አለኝም “ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውሃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።