ዳዊትና እስራኤል ሁሉ ከመዘምራን ጋር በበገና፥ በመሰንቆና በከበሮ፥ በጸናጽልና በመለከት በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይዘምሩ ነበር።
መዝሙር 68:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተማቸው በረሃ ትሁን፥ በድንኳኖቻቸውም የሚቀመጥ አይገኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም መዘምራን ከፊት፣ መሣሪያ የሚጫወቱ ከኋላ ሆነው ሲሄዱ፣ ከበሮ የሚመቱ ቈነጃጅትም በመካከላቸው ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምላክ ሆይ ጉዞህን አዩት፥ የአምላኬና የንጉሤ ንግደት ወደ ቤተ መቅደስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘማሪዎች ከፊት፥ ሙዚቀኞች ከኋላ፥ አታሞ የሚመቱ ልጃገረዶች ከመካከል፥ ሆነው ይታያሉ። |
ዳዊትና እስራኤል ሁሉ ከመዘምራን ጋር በበገና፥ በመሰንቆና በከበሮ፥ በጸናጽልና በመለከት በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይዘምሩ ነበር።
በዚያን ጊዜም ደናግሉ በዘፈን ደስ ይላቸዋል፤ ጐበዛዝቱና ሽማግሌዎቹም በአንድ ላይ ደስ ይላቸዋል፤ እኔም ልቅሶአቸውን ወደ ደስታ እመልሳለሁ፤ ከኀዘናቸውም ደስ አሰኛቸዋለሁ።
የእስራኤል ድንግል ሆይ እንደ ገና እሠራሻለሁ፤ አንቺም ትሠሪያለሽ፤ እንደ ገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ከዘፋኞች ጋር ትወጫለሽ።
ዮፍታሔም ወደ መሴፋ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ እነሆም፥ ልጁ ከበሮ ይዛ እየዘፈነች ልትቀበለው ወጣች፤ ለእርሱም የሚወድዳት አንዲት ብቻ ነበረች። ከእርስዋም በቀር ወንድ ወይም ሴት ሌላ ልጅ አልነበረውም።
እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ፥ እየዘመሩና እየዘፈኑ፥ እልልም እያሉ ከበሮና አታሞ ይዘው ዳዊትን ሊቀበሉ ሴቶች ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ወጡ።