ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤትን ያድርጉ፥ በደስታም ደስ ይበላቸው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰዎች ያመስግኑህ፤ ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ።
መንገድህንም በምድር፥ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ማዳንህን እናውቅ ዘንድ።
አምላክ ሆይ፥ ሕዝቦች ያመስግኑህ፤ ሕዝቦች ሁሉ ያመስግኑህ።
አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፥ ሰውነቴ አልቃለች፤ ፊትህንም ከእኔ አትመልስ፥ ወደ ጕድጓድም እንደሚወርዱ አልሁን።
እግዚአብሔር በቅዱስ ቦታው ለድሃ አደጎች አባት፥ ለባልቴቶችም ዳኛ ነው።
እርሱም፥ “የያዕቆብን ነገዶች እንደገና እንድታስነሣ፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ወደ አባቶች ቃል ኪዳን እንድትመልስ ባርያዬ ትሆን ዘንድ ለአንተ እጅግ ታላቅ ነገር ነውና፥ እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኀኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ” ይላል።
ስለዚህ ወላጂቱ እስከምትወልድበት ጊዜ ድረስ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ የቀሩትም ወንድሞቹ ወደ እስራኤል ልጆች ይመለሳሉ።