ዳዊትም ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም ያሉትን አገልጋዮቹን ሁሉ፥ “ተነሡ እንሽሽ፤ ከአቤሴሎም እጅ የምንድንበት የለንምና፤ ፈጥኖ እንዳይዘን፥ ክፉም እንዳያመጣብን፤ ከተማዪቱንም በሰልፍ ስለት እንዳይመታ ፈጥናችሁ እንሂድ” አላቸው።
መዝሙር 64:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ የመረጥኸው በአደባባዮችህም ለማሳደር የተቀበልኸው ብፁዕ ነው፤ አቤቱ፥ ከቤትህ በረከት ጠገብን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሸምቀው ንጹሑን ሰው ይነድፉታል፤ ድንገት ይነድፉታል፤ አይፈሩምም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ሰይፍ ምላሳቸውን አሰሉ፥ እንደ ፍላጻ መራራ ነገርን ለመወርወር፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ያለ ፍርሀት ንጹሑን ሰው ሸምቀው ይነድፉታል። |
ዳዊትም ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም ያሉትን አገልጋዮቹን ሁሉ፥ “ተነሡ እንሽሽ፤ ከአቤሴሎም እጅ የምንድንበት የለንምና፤ ፈጥኖ እንዳይዘን፥ ክፉም እንዳያመጣብን፤ ከተማዪቱንም በሰልፍ ስለት እንዳይመታ ፈጥናችሁ እንሂድ” አላቸው።
ጠላቶቻችንም፥ “ወደ መካከላቸው እስክንመጣና እስክንገድላቸው ድረስ፥ ሥራቸውንም እስክናስተጓጕል ድረስ አያውቁም፤ አያዩም” አሉ።
ሊቃነ ካህናትና ሎሌዎቻቸውም ባዩት ጊዜ፥ “ስቀለው! ስቀለው!” እያሉ ጮሁ፤ ጲላጦስም፥ “እናንተ ራሳችሁ ውሰዱና ስቀሉት፤ እኔስ በእርሱ ላይ በደል አላገኘሁበትም” አላቸው።
ሳኦልም ዳዊትን ከግንብ ጋር ያጣብቀው ዘንድ ጦሩን ወረወረ፤ ዳዊትም ከሳኦል ፊት ዘወር አለ፤ ጦሩም በግንቡ ውስጥ ተተከለ፤ በዚያም ሌሊት ዳዊት ሸሸቶ አመለጠ።