ንጹሕንም በስውር ለመግደል ቀስትን ገተሩ፤ በድንገት ይነድፏቸዋል አይፈሩምም።
እንግዲህ፣ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፤ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ።
ቸርነትህ ከሕይወት ይሻላልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ አመሰግንሃለሁ፤ ለጸሎትም እጆቼን ወደ አንተ እዘረጋለሁ።
ወይናቸውንና በለሳቸውን መታ፥ የሀገራቸውንም ዛፍ ሁሉ ሰበረ።
በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ፥ በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ።
የስሙን ክብር ለእግዚአብሔር አምጡ፥ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
ተራሮች አንተን አይተው ተጨነቁ፣ የውኃ ሞገድ አልፎአል፣ ቀላዩም ድምፁን ሰጥቶአል፥ እጁንም ወደ ላይ አንሥቶአል።