ከሰማይ ልኮ አዳነኝ፥ ለረገጡኝም ውርደትን ሰጣቸው፤ እግዚአብሔር ቸርነቱንና ጽድቁን ላከ።
ፍርሀት በሚይዘኝ ጊዜ፣ መታመኔን በአንተ ላይ አደርጋለሁ።
የሚዋጉኝ በዝተዋልና ቀኑን ሁሉ ጠላቶቼ ረገጡኝ።
ፍርሀት ቢይዘኝ እንኳ በአንተ እተማመናለሁ።
ኢዮሣፍጥም ፈራ፤ እግዚአብሔርንም ሊፈልግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም አወጀ።
አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።
ነፍሴን የሚሹ ሁሉ ይፈሩ ይጐሳቈሉም፤ ክፋትን በእኔ ላይ የሚመክሩ ይፈሩ፥ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ።
ዳዊትም ተነሣ በዚያም ቀን ከሳኦል ፊት ሸሸ፤ ወደ ጌትም ንጉሥ ወደ አንኩስ መጣ።
ዳዊትም ይህን ቃል በልቡ አኖረ፤ የጌትንም ንጉሥ አንኩስን እጅግ ፈራ።
ስለ ወንዶችና ስለ ሴቶች ልጆቻቸውም የሕዝቡ ሁሉ ልብ አዝኖ ነበርና ሕዝቡ ሊወግሩት ስለ ተናገሩ ዳዊት እጅግ ተጨነቀ፤ ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ራሱን አጽናና።