ዳዊትም መልእክተኞችን ልኮ አስመጣት፤ ወደ እርሱም ገባች፤ ከርኵሰቷም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ፤ ወደ ቤቷም ተመለሰች።
መዝሙር 51:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልብህ ኀጢአትን ያስባል፤ እንደ ተሳለ ምላጭ ሽንገላን አደረግህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በደሌን ፈጽሞ ዕጠብልኝ፤ ከኀጢአቴም አንጻኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ቤርሳቤህ ከገባ በኋላ ነቢዩ ናታን ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደሌን ሁሉ አጥበህ አስወግድልኝ፤ ከኃጢአቴም አንጻኝ። |
ዳዊትም መልእክተኞችን ልኮ አስመጣት፤ ወደ እርሱም ገባች፤ ከርኵሰቷም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ፤ ወደ ቤቷም ተመለሰች።
እግዚአብሔርም ነቢዩ ናታንን ወደ ዳዊት ላከ፤ ወደ እርሱም መጥቶ አለው፥ “በአንድ ከተማ አንዱ ባለጠጋ፥ አንዱም ድሃ የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ።
ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ፤ እናንተም ከርኵሰታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ፤ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አነጻችኋለሁ።
ልብሱ ወይም ድሩ ወይም ማጉ ወይም ከቆዳ የተደረገው ነገር ከታጠበ በኋላ ደዌው ቢለቅቀው ሁለተኛ ጊዜ ይታጠባል፤ ንጹሕም ይሆናል።
እንግዲህ እናንተ እንዲህ ስትሆኑ እነማን ናችሁ? ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፤ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችኋልም።