መዝሙር 50:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጽድቁን መሥዋዕት፥ መባውንም፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በወደድህ ጊዜ፥ ያንጊዜ በመሠዊያህ ላይ ፍሪዳዎችን ይሠዋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አፍህን ለክፋት አዋልህ፤ አንደበትህም ሽንገላን ጐነጐነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አፍህ ክፋትን አበዛ፥ አንደበትህም ሽንገላን ተበተበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ክፉ ነገር ለመናገር ለአንደበትህ ነጻነትን ሰጠኸው፤ ንግግርህም ሁሉ ሽንገላ ብቻ ነው። |
በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፥ ጕሮሮኣቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
እያንዳንዱ በባልንጀራው ላይ ይሣለቃል በእውነትም አይናገርም፤ ሐሰት መናገርንም ምላሳቸው ተምሮአል፤ በደሉ መመለስንም እንቢ አሉ።
ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”