አቤቱ፥ በጽድቅህ ምራኝ፤ ስለ ጠላቶቼ መንገዴን በፊትህ አቅና።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከጠላቶቼ የተነሣ፣ በጽድቅህ ምራኝ፤ መንገድህንም በፊቴ አቅናልኝ።
እኔ ግን በቸርነትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፥ አንተን በመፍራት ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! የሚጠባበቁኝ ጠላቶቼ ብዙዎች ናቸው! ስለዚህ ፈቃድህን እንዳደርግ ምራኝ፤ መንገድህንም በፊቴ አቅናልኝ።
ነገር ግን በዚህ ነገር ለእግዚአብሔር ጠላቶች መነሣሣት ምክንያት አድርገሃልና ስለዚህ ደግሞ የተወለደልህ ልጅ ፈጽሞ ይሞታል” አለው።
አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ። የልቤን ዐሳብ ሁሉ ከሩቁ ታስተውላለህ።
ኀጢአታቸው የተተወላቸው፥ በደላቸውንም ሁሉ ያልቈጠረባቸው ብፁዓን ናቸው።
ፍርሃትና እንቅጥቅጥ ያዙኝ፥ ጨለማም ሸፈነኝ።
አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላካችን ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።
ዐይኖችህም አቅንተው ይዩ፥ ሽፋሽፍቶችህም ወደ እውነት ያመልክቱ።
እኔም፦ ከዐይንህ ፊት ተጣልሁ፤ ነገር ግን ወደ ቅዱስ መቅደስህ ደግሞ እመለከታለሁን? አልሁ።
በነቢዩ በኢሳይያስ “ ‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጥርጊያውንም አቅኑ’ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ” የተባለለት ይህ ነውና።
አንካሳነታችሁ እንዲድንና እንዳትሰነካከሉ ለእግሮቻችሁ የቀና መንገድን አድርጉ።