መዝሙር 48:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዓለም የደከመ ለዘለዓለም ይድናል፥ ጥፋትን አያይምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ሆይ፤ በቤተ መቅደስህ ውስጥ ሆነን፣ ምሕረትህን እናስባለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ሰማን እንዲሁ አየን በሠራዊት ጌታ ከተማ፥ በአምላካችን ከተማ፥ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያጸናታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! በመቅደስህ ውስጥ ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህ እናስባለን። |
እኔም መጥቼ በዐይኔ እስካይ ድረስ የነገሩኝን አላመንሁም ነበር ፤ እነሆም፥ እኩሌታውን አልነገሩኝም ነበር፤ በሀገሬ ሳለሁ ከነገሩኝ ይልቅ የበለጠ መልካም ተጨማሪ አየሁ።
እንደ ተገደሉና በመቃብር ውስጥ እንደ ተጣሉ፥ ለዘለዓለም እንደማታስባቸው በሙታን መካከል የተጣልሁ ሆንሁ፤ እነርሱ ከእጅህ ርቀዋልና።
ከወደ ኋላህም ሳቡህ፥ በሽቱህ መዓዛም እንሮጣለን፤ ንጉሡ ወደ እልፍኙ አገባኝ፤ በአንቺ ደስ ይለኛል፥ ሐሤትም እናደርጋለን፤ ከወይን ጠጅ ይልቅ ጡቶችሽን እንወዳለን፤ አንቺንም መውደድ የተገባ ነው።
የአስሬሞትም ሸለቆ ሁሉ እስከ ቄድሮን ወንዝ ድረስ በምሥራቅ በኩል እስካለው እስከ ፈረስ በር ማዕዘን ድረስ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ከእንግዲህም ወዲህ ለዘለዓለም አይነቀልም፤ አይፈርስምም።