መዝሙር 44:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልቤ መልካም ነገርን ተናገረ፥ እኔም ሥራዬን ለንጉሥ እናገራለሁ፤ አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ሆይ፤ በጆሯችን ሰምተናል፤ አባቶቻችን በቀድሞ ዘመን፣ እነርሱ በነበሩበት ዘመን፣ ያደረግኸውን ነግረውናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች ትምህርት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! በጥንት ዘመን ያደረግኸውን ሁሉ በጆሮአችን ሰማን፤ የቀድሞ አባቶቻችንም በዘመናቸው ስላደረግሃቸው ድንቅ ነገሮች ሁሉ ነግረውናል። |
ለያዕቆብ ያቆመውን ምስክር፥ ለእስራኤልም የሠራውን ሕግ፥ ለአባቶቻችን ያዘዘውን ለልጆቻቸው ይነግሩ ዘንድ፥
ጌዴዎንም፥ “ጌታዬ ሆይ! እሺ፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን? አባቶቻችንስ፦ እግዚአብሔር ከግብፅ አውጥቶናል ብለው ይነግሩን የነበረ ተአምራት ወዴት አለ? አሁን ግን እግዚአብሔር ትቶናል፤ በምድያም እጅም አሳልፎ ሰጥቶናል” አለው።