መዝሙር 40:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበደልን ነገር በእኔ አወጡ። የተኛ ሰው ከእንግዲህ ወዲህ አይነቃምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላኬ ሆይ፤ ፈቃድህን ላደርግ እሻለሁ፤ ሕግህም በልቤ ውስጥ አለ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ እንዲህ አልሁ፦ “እነሆ፥ መጣሁ፥ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአል፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላኬ ሆይ! ፈቃድህን መፈጸም እወዳለሁ፤ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው” አልኩ። |
ቃልህ ተገኝቶአል፤ እኔም በልችዋለሁ፤ አቤቱ! የሠራዊት አምላክ ሆይ! ቃልህን የከዱ ሰዎችን አጥፋቸው፤ ስምህ በእኔ ላይ ተጠርትዋልና፥ ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ።
ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የእኔስ መብል የላከኝን የአባቴን ፈቃድ አደርግ ዘንድ፥ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።
ልጁ በብዙዎች ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ ያወቃቸውንና የመረጣቸውን እነርሱን ልጁን ይመስሉ ዘንድ አዘጋጅቶአቸዋል።
እናንተ ራሳችሁም በእኛ የተላከች የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ ያውቃሉ፤ ይህቺውም የተጻፈች በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ ነው እንጂ በቀለም አይደለም፤ በሥጋ ልብ ሠሌዳነት ነው እንጂ በድንጋይ ሠሌዳም አይደለም።