መታመኛው የእግዚአብሔር ስም የሆነ፥ ወደ ከንቱ ነገር፥ ወደ ቍጣና ወደ ሐሰትም፥ ያልተመለከተ ሰው ብፁዕ ነው።
“እግዚአብሔር ሆይ፤ የሕይወቴን ፍጻሜ፣ የዘመኔንም ቍጥር አስታውቀኝ፤ ዐላፊ ጠፊ መሆኑንም ልረዳ።
ልቤም በውስጤ ሞቀብኝ፥ ከማሰቤም የተነሣ እሳት ነደደ፥ በአንደበቴም ተናገርሁ፦
“ጌታ ሆይ! መጨረሻዬንና የቀኖቼን ብዛት እንዳውቅ አድርገኝ፤ ዕድሜዬም ምን ያኽል አጭር እንደ ሆነ ንገረኝ።”
“በመቃብር ውስጥ ምነው በጠበቅኸኝ ኖሮ! ቍጣህ እስኪበርድም ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ! እስከምታስበኝም ምነው ቀጠሮ በሰጠኸኝ ኖሮ!
እህልን ከምድር ያወጣ ዘንድ፥ ለምለሙን ለሰው ልጆች አገልግሎት፥ ሣርንም ለእንስሳ ያበቅላል።
እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።