አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን? ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው።
ወገቤ እንደ እሳት ነድዷል፤ ሰውነቴም ጤና የለውም።
እጅግ ጐሰቈልሁ ተዋረድሁም፥ ሁልጊዜም በትካዜ እመላለሳለሁ።
ትኲሳት ወገቤን እያቃጠለው ነው፤ ሁለመናዬም ጤና አጣ።
ንጉሡንም፥ “ንጉሡ ለዘለዓለም ይኑር፤ የአባቶች መቃብር ያለባት ከተማ ተፈትታለችና፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋልና ፊቴ ስለ ምን አያዝን?” አልሁት።
ከታላቁ ደዌ ኀይል የተነሣ ልብሴ ተበላሸች፤ የልብሴ ክሳድ አነቀችኝ፥ ቀሚሴም በአንገቴ ተጣበቀ።
ሥጋዬ በትልና በመግል በስብሶአል፥ ቍስሌን በገል እያከክሁ አለቅሁ። ዐመድም ሆንሁ።
ኀጢአትህን ሁሉ ይቅር የሚልልህ፤ ደዌህንም ሁሉ የሚፈውስህ፥
እግዚአብሔር በቀን ይቅርታውን ያዝዛል፥ በሌሊትም እርሱን ይናገራል፤ ከእኔ ዘንድ የሕይወቴ ብፅዐት ለእግዚአብሔር ነው።
ለእግዚአብሔርም ክብር ስለ አልሰጠ ያንጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቀሠፈው፤ ተልቶም ሞተ።