መዝሙር 37:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአቴ ከራሴ ጠጕር በዝቷልና፥ እንደ ከባድ ሸክምም በላዬ ከብዶአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤ እርሱም የልብህን ፍላጎት ሁሉ ይሰጥሃል። |
በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በወንድሞች መካከል ነው። ከጥላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀመጥሁ፥ ፍሬውም ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው።
በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ትታመናለህ፤ በምድርም በረከት ላይ ያወጣሃል፤ የአባትህ የያዕቆብንም ርስት ይመግብሃል፤ የእግዚአብሔር አፍ እንደዚህ ተናግሮአልና።
እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ የመረጣችሁኝ አይደለም፤ እንድትሄዱ፥ ፍሬም እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም እንዲኖር፤ አብንም በስሜ የምትለምኑት ነገር ቢኖር ሁሉን እንዲሰጣችሁ ሾምኋችሁ።
እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።