እኔንስ ይገርፉኝ ዘንድ አቈዩኝ፥ ቍስሌ ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።
የክፉዎች ክንድ ይሰበራልና፣ ጻድቃንን ግን እግዚአብሔር ደግፎ ይይዛቸዋል።
የክፉዎች ንድ ትሰበራለችና፥ ጌታ ግን ጻድቃንን ይደግፋቸዋል።
የክፉዎች ኀይል ይሰበራል ጻድቃንን ግን እግዚአብሔር ያበረታቸዋል።
የኃጥኣንን ብርሃናቸውን ከልክለሃልን? የትዕቢተኞችንስ ክንድ ሰብረሃልን?
አንደበታቸው በላያቸው ደከመ፥ የሚያዩአቸውም ሁሉ ደነገጡ።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፤ እረዳህማለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
እነሆ፥ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ ያዕቆብ፤ ነፍሴ የተቀበለችው ምርጤ እስራኤልም፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያመጣል።
የሞአብ ቀንድ ተሰበረ፤ እጁም ተቀጠቀጠ ይላል እግዚአብሔር።
ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው፤
እነሆ፥ ዘርህንም፥ የአባትህንም ቤት ዘር የማጠፋበት ዘመን ይመጣል፤