መዝሙር 34:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ትፈርድልኛለህ? ነፍሴን ከክፉ ሥራቸው፥ ብቸኝነቴንም ከአንበሶች አድናት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቃን ሲጮኹ፣ እግዚአብሔር ይሰማቸዋል፤ ከመከራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ የጌታ ፊት ክፉን በሚያደርጉ ላይ ተነሥቶአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጻድቃን ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፤ እርሱም ይሰማቸዋል፤ ከችግራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል። |
እነሆ፥ እግዚአብሔር የዋሁን ሰው አይጥለውም፥ የኀጢኣተኞችንም እጅ አያበረታም። የዝንጉዎችንም መባ አይቀበልም።
ፊቴንም በዚያ ሰው ላይ አደርጋለሁ፤ እንዲጠፋም አደርገዋለሁ፤ ከሕዝቤም መካከል አስወግደዋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
በጠላቶቻቸውም ፊት ተማርከው ቢሄዱ በዚያ ሰይፍን አዝዛታለሁ፤ እርስዋም ትገድላቸዋለች፤ ዐይኔንም ለመልካም ሳይሆን ለክፋት በእነርሱ ላይ እጥላለሁ።”