እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ፥ ዕወቁም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ብፁዕ ነው።
ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፍራው፤ በዓለም የሚኖር ሕዝብ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጥ።
ምድር ሁሉ ጌታን ትፍራው፥ በዓለም የሚኖሩ ሁሉ ይደንግጡ።
በምድርም የምትኖሩ ሁሉ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔርን አክብሩ።
ስለዚህ ሰዎች ይፈሩታል፤ በልባቸውም ጠቢባን የሆኑ ሁሉ ይፈሩታል።”
አቤቱ፥ በሕዝብህ ፊት በወጣህ ጊዜ፥ በምድረ በዳም ባለፍህ ጊዜ፥
እግዚአብሔር ለዘለዓለም በውኑ ይጥላልን? እንግዲህስ ይቅርታውን አይጨምርምን?
አምላካችን በእውነት የሚያቃጥል እሳት ነውና።