ዳዊትና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣሪያዎች በበገናና በመሰንቆ፥ በከበሮና በነጋሪት፥ በጸናጽልና በዕንዚራ በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይጫወቱ ነበር።
መዝሙር 33:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴም በእግዚአብሔር ትከብራለች፥ ገሮችም ይስሙ፥ ደስም ይበላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፤ ዐሥር አውታር ባለውም በገና ዘምሩለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታን በመሰንቆ አመስግኑት፥ ዐሥር አውታርም ባለው በገና ዘምሩለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፤ ዐሥር አውታር ባለውም በገና ዘምሩለት። |
ዳዊትና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣሪያዎች በበገናና በመሰንቆ፥ በከበሮና በነጋሪት፥ በጸናጽልና በዕንዚራ በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይጫወቱ ነበር።
ዳዊትም በዜማ ዕቃ፥ በመሰንቆና በበገና፥ በጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ ድምፃቸውንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን “ወንድሞቻችሁን ሹሙ” ብሎ ለሌዋውያን አለቆች ተናገረ።
እንዲሁ እስራኤል ሁሉ በይባቤ፥ ቀንደ መለከትና እንቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽልና መሰንቆም፥ በገናም እየመቱ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።
ከኤዶትም የኤዶትም ልጆች፤ ጎዶልያስ፥ ሱሪ፥ የሻያ፥ ሰሜኢ፥ ሐሸብያ፥ መታትያ፥ እነዚህ ስድስቱ ከአባታቸው ከኤዶትም ጋር በበገና እየዘመሩ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።
እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና፥ በመሰንቆም ከአባታቸው ጋራ የእግዚአብሔርን ቤት ለማገልገል ወደ ንጉሡ ቀርበው ያመሰግኑ ነበር። አሳፍም ኤዶትምም ኤማንም ያመሰግኑ ነበር።
መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።