እግዚአብሔርን ሁልጊዜ አመሰግነዋለሁ። ምስጋናውም ዘወትር በአፌ ነው።
ጻድቃን ሆይ፤ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ቅኖች ሊወድሱት ይገባቸዋል።
የዳዊት መዝሙር። ጻድቃን ሆይ፥ በጌታ ደስ ይበላችሁ፥ ለቅኖች ምስጋና ይገባል።
ጻድቃን ሆይ! በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ቅኖች ሊያመሰግኑት ይገባል።
ትእዛዝህን አሰላሰልሁ፥ መንገድህንም እፈልጋለሁ።
የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኚ፥
የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥ የልቡም ዐሳብ ለልጅ ልጅ ነው።
የክፉዎች መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ ነው፤ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው።
መጽሐፍ እንዲህ እንዳለ “አንድ ስንኳ ጻድቅ የለም።
በአንድ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኀጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንድ ሰው መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።
ዘወትር በጌታችን ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላችኋለሁ፦ ደስ ይበላችሁ።