መዝሙር 31:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አስተምርሃለሁ፥ በምትሄድባትም በዚች መንገድ አጸናሃለሁ። ዐይኖቼን በአንተ ላይ አጸናለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለጠላት አሳልፈህ አልሰጠኸኝም፤ ነገር ግን እግሮቼን ሰፊ ቦታ ላይ አቆምሃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መከራዬን አይተሃልና፥ ነፍሴንም ከጭንቀት አድነሃታልና በምሕረትህ ደስ ይለኛል ሐሤትም አደርጋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለጠላቶች አሳልፈህ አልሰጠኸኝም፤ ነገር ግን ሰፊ መንገድ ከፈትክልኝ። |
አንተን ግን ከጠላትህ አፍ አድኖሃል፥ በበታችህም ጥልቅ ባሕር፥ ፈሳሽ ምንጭም አለ፥ ማዕድህም በስብ ተሞልታ ትወርዳለች።
ግብፃውያንንም በጨካኝ ጌቶች እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ጨካኞች ነገሥታትም ይገዟቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ወደ አባቶቻችንም አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ቃላችንን ሰማ፤ ጭንቀታችንንም፥ ድካማችንንም፥ ግፋችንንም አየ፤
አንዱ ሽሁን እንዴት ያሳድዳቸዋል? ሁለቱስ ዐሥሩን ሽህ እንዴት ያባርሩአቸዋል? እግዚአብሔር ፍዳውን አምጥቶባቸዋልና። አምላካችንም አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና።
እግዚአብሔር ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፤ እመታህማለሁ፤ ራስህንም ከአንተ እቈርጠዋለሁ፤ ሬሳህንና የፍልስጥኤማውያንንም ሠራዊት ሬሶች ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ዛሬ እሰጣለሁ። ምድር ሁሉ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር እንዳለ ያውቃሉ፤
አቢሳም ዳዊትን፥ “ዛሬ እግዚአብሔር ጠላትህን በእጅህ አሳልፎ ሰጥቶታል፤ አሁንም እኔ በጦር አንድ ጊዜ ከምድር ጋር ላጣብቀው፤ ሁለተኛም አልደግመውም” አለው።