መዝሙር 31:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ጻድቅ ሁሉ በምቹ ጊዜ ወደ አንተ ይጸልያል፤ ነገር ግን ብዙ የጥፋት ውኃ ወደ አንተ አይቀርብም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለከንቱ ጣዖታት ስፍራ የሚሰጡትን ጠላሁ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ታመንሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእጅህ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ፥ የእውነት አምላክ አቤቱ፥ ተቤዥተኸኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዋጋቢሶች ለሆኑ ጣዖቶች የሚሰግዱትን ሁሉ ትጠላለህ፤ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ። |
በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ሸሽጎኛልና፥ በድንኳኑም መሸሸጊያ ሰውሮኛልና፥ በዓለትም ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና።
አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ በሥጋም በነበረበት ጊዜ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን ስለ ሠራው ሁሉ መልስ ሳይሰጥ ፈጣሪህን አስብ።
እግዚአብሔርን ሲያውቁት እንደ እግዚአብሔርነቱ አላከበሩትም፤ አላመሰገኑትምም፤ ነገር ግን ካዱት፤ በአሳባቸውም ረከሱ፤ ልቡናቸውም ባለማወቅ ጨለመ።
አሕዛብም የሚሠዉ ለአጋንንት ነው እንጂ ለእግዚአብሔር አይደለም፤ ነገር ግን የአጋንንት ተባባሪዎች እንድትሆኑ አልፈቅድላችሁም።
ለጣዖታት የተሠዋውን ስለመብላት ግን ጣዖት ሁሉ በዓለም ከንቱ እንደሆነ፥ ከአንድ እግዚአብሔርም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።