አቤቱ፥ ተቀብለኸኛልና፥ የጠላቶቼ መዘባበቻ አላደረግኸኝምና አመሰግንሃለሁ።
እናንተ ኀያላን፣ ለእግዚአብሔር ስጡ፤ ክብርንና ብርታትን ለእግዚአብሔር ስጡ።
ከድንኳን በሚወጣበት ጊዜ፥ የዳዊት መዝሙር። የአምላክ ልጆች ሆይ፥ ለጌታ አምጡ። ክብርንና ምስጋናን ለጌታ አምጡ።
እናንተ የሰማይ መላእክት ሁሉ፥ ክብርና ኀይል የእግዚአብሔር ነው በሉ።
እግዚአብሔር ጽዮንን አድኗታልና፥ የይሁዳም ከተሞች ይሠራሉና፤ በዚያም ይቀመጣሉ ይወርሷታልም።
እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመቅሠፍትህም ደንግጠናልና።
ለአንቺም የማይገዙ ነገሥታት ይሞታሉ፤ እነዚያም አሕዛብ ፈጽመው ይጠፋሉ።