እንዲህም አለ፥ “ይሁዳ ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ፥ አንተም ንጉሡ ኢዮሣፍጥ! ስሙ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል፦ ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእናንተ አይደለምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተነሣ አትፍሩ፤ አትደንግጡም።
መዝሙር 27:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኃጥኣን ጋር ነፍሴን አትውሰዳት፤ ክፋትም በልባቸው እያለ ከባልንጀራቸው ጋር ሰላምን ከሚናገሩ ዐመፅ አድራጊዎች ጋር አትጣለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰራዊት ቢከብበኝ እንኳ፣ ልቤ አይፈራም፤ ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ፣ ልበ ሙሉ ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሠራዊትም ቢከብበኝ ልቤ አይፈራም፥ ጦርነትም ቢነሣብኝ በዚህ እተማመናለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ ሠራዊት ቢከበኝም አልፈራም፤ ጠላቶቼ በጦርነት ቢያጠቁኝ እንኳ በእግዚአብሔር መተማመኔን አልተውም። |
እንዲህም አለ፥ “ይሁዳ ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ፥ አንተም ንጉሡ ኢዮሣፍጥ! ስሙ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል፦ ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእናንተ አይደለምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተነሣ አትፍሩ፤ አትደንግጡም።
ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፤ አንተ በከንቱ የሚጠሉኝን ሁሉ መትተሃልና፥ የኃጥኣንንም ጥርስ ሰብረሃልና።
መድኀኒትን ከጽዮን ለእስራኤል ማን ይሰጣል? እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤትን ያደርጋል።
ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ እንድፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፤ ዐሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።