መዝሙር 25:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን በየዋህነቴ እኖራለሁ፤ አቤቱ፦ አድነኝ ይቅርም በለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአቴ ታላቅ ነውና፣ ስለ ስምህ ይቅር በልልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ በደሌ ብዙ ነውና ስለ ስምህ ይቅር በለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ስምህ ክብር እጅግ የበዛውን ኃጢአቴን ይቅር በልልኝ። |
ለብዙ ሺህ ጽድቅን የሚጠብቅ፥ ቸርነትን የሚያደርግ፥ አበሳንና መተላለፍን፥ ኀጢአትንም ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችንም ኀጢአት በልጆች፥ እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድም በልጅ ልጆች የሚያመጣ አምላክ ነው” ሲል አወጀ።
አቤቱ! ኀጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኀጢአት ሠርተናልና ኀጢአታችን ተቃውሞናል፤ ነገር ግን ስለ ስምህ ብለህ አድርግ።
ነገር ግን በመካከላቸው በአሉ፥ ከግብጽም ምድር አወጣቸው ዘንድ በፊታቸው በተገለጥሁላቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።
“ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ቤት ሆይ! በገባችሁባቸው በአሕዛብ መካከል ስላረከሳችሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ነው እንጂ ስለ እናንተ የምሠራ አይደለሁም።
ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋው በበደላችን መጠን የሆነብን አይደለም፤ በአንድ ሰው በደል ብዙዎች ከሞቱ፥ እንግዲህ በእግዚአብሔር ጸጋ፥ በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት በሰጠን ሀብቱ ሕይወት በብዙዎች ላይ እንዴት እጅግ ይበዛ ይሆን?