በመከራህ ቀን እግዚአብሔር ይስማህ፤ የያዕቆብ አምላክ ስምም ይቁምልህ።
ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያውጃሉ።
ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፤ የሰማይ ጠፈርም፥ የእጁን ሥራ ያውጃል።
በዚያን ጊዜ አያት፥ ገለጣትም፤ አዘጋጃትም፥ አከበራት፥ ደግሞም መረመራት።
ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ እግዚአብሔርም ሰማው፥ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።
እነሆ፥ እውነትን ወደድህ፤ የማይነገር ስውር ጥበብህን አስታወቅኸኝ።
የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን፥ አንተ የሠራሃቸውን፥ ጨረቃንና ከዋክብትን እናያለንና።