ከሕዝቡም ጋር ተማክሮ በሠራዊቱ ፊት የሚሄዱትን፥ “ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ” የሚሉትንም፥ በቅድስና የሚያመሰግኑትን፥ ለእግዚአብሔርም የሚዘምሩትን መዘምራን አቆመ።
መዝሙር 18:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃላቸው ወደ ምድር ሁሉ ወጣ። ነገራቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደረሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሞት ገመድ ዐነቀኝ፤ ምናምንቴ ነገርም አጥለቀለቀኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምስጋና የሚገባውን ጌታን እጠራለሁ፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሞት ጣር ከበበኝ፤ የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ። |
ከሕዝቡም ጋር ተማክሮ በሠራዊቱ ፊት የሚሄዱትን፥ “ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ” የሚሉትንም፥ በቅድስና የሚያመሰግኑትን፥ ለእግዚአብሔርም የሚዘምሩትን መዘምራን አቆመ።
ዝማሬውንና ምስጋናውንም በጀመሩ ጊዜ ይሁዳን ሊወጉ በመጡት በአሞንና በሞዓብ ልጆች በሴይርም ተራራ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር ኀይልን ሰጣቸው፤ እነርሱም ተመቱ።
ሽማግሎች ይደነግጣሉ፤ እንደምትወልድ ሴትም ምጥ ይይዛቸዋል፤ እርስ በርሳቸውም ይገዳደላሉ፤ ይደነቃሉ፤ ፊታቸውም እንደ እሳት ይንበለበላል።
ይህንም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፤ ከእርሱም ጋር ብዙ ሕዝብ ሰይፍና ጐመድ ይዘው ከካህናት አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሎች ዘንድ መጡ።
በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ለሕዝቡ “ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ ወጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስቀመጥ ሳለሁ አልያዛችሁኝም።