መሰወሪያውን ጨለማ አደረገ፤ በዙሪያውም ድንኳኑ፤ ውኃዎች በደመናዎች ውስጥ ጠቈሩ።
አሳድደው ደረሱብኝ፤ ከበቡኝም፤ መሬት ላይ ሊዘርሩኝም አፈጠጡብኝ።
አሁንም እርምጃችንን ከበቡ፥ ዓይናቸውን ወደ ምድር ዝቅ ዝቅ አደረጉ።
ጠላቶቼ አስጨነቁኝ፤ ከበባም አደረጉብኝ፤ ወደ መሬት ሊጥሉኝም ዐይናቸውን ጣሉብኝ።
እንደማይሰማ ሰው፥ በአፉም መናገር እንደማይችል ሰው ሆንሁ።
የኀይላቸው ትምክሕት አንተ ነህና፥ በይቅርታህም ቀንዳችን ከፍ ከፍ ይላልና።
ሳኦልና ሰዎቹም በተራራው በአንድ ወገን ሄዱ፤ ዳዊትና ሰዎቹም በተራራው በሌላው ወገን ሄዱ። ዳዊትም ከሳኦል ፊት ያመልጥ ዘንድ ተሰውሮ ነበር። ሳኦልና ሰዎቹ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመያዝ ከብበዋቸው ነበርና።