ከሚያጐሳቍሉኝ ኃጥኣን ፊት፥ ጠላቶቼ ግን ነፍሴን ተመለከትዋት፤
ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ አንደበቴም ሐሤት አደረገ፤ ሥጋዬም ያለ ሥጋት ዐርፎ ይቀመጣል፤
ስለዚህ ልቤን ደስ አለው ነፍሴም ሐሴት አደረገች፥ ሥጋዬም ደግሞ በተስፋ ታድራለች፥
ስለዚህ ልቤ ተደስቶ ይፈነጥዛል፤ ሰውነቴም ያለ ስጋት ያርፋል።
አቤቱ፥ ልመናዬን ቸል አትበል፥
እንደ ሞተ ሰው ከልብ ረሱኝ፥ እንደ ጠፋ ዕቃም ሆንሁ።
እንደሚቀልጥ ሰም ያልቃሉ፤ እሳት ወደቀች፥ ፀሐይንም አላየኋትም።
ኃጥእ በክፋቱ ይወገዳል፤ በቸርነቱ የሚታመን ግን ጻድቅ ነው።
ሙታን ይነሣሉ፤ በመቃብር ያሉም ይድናሉ። በምድርም የሚኖሩ ደስ ይላቸዋል፤ ከአንተ የሚገኝ ጠል መድኀኒታቸው ነውና፤ የኃጥኣንንም ምድር ታጠፋለህ።
ስለዚህ ልቤን ደስ አለው፤ አንደበቴም ሐሤት አደረገ፤ ሥጋዬም ደግሞ በተስፋው አደረ።