ጻድቃን በክብሩ ይመካሉ፤ በመኝታቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ።
ቅዱሳን በዚህ ክብር ይጓደዱ፤ በመኝታቸውም ላይ እልል እያሉ ይዘምሩ።
ቅዱሳን በክብር ይመካሉ፥ በምንጣፋቸውም ላይ ሐሤትን ያደርጋሉ።
የእግዚአብሔር ሕዝቦች በድል አድራጊነታቸው ደስ ይበላቸው፤ ሌሊቱን በሙሉ በደስታ ይዘምሩ።
ዳዊትና የእስራኤልም ቤት ሁሉ በእልልታ ቀንደ መለከት እየነፉ የእግዚአብሔርን ታቦት አመጡአት።
ነገር ግን በሌሊት ጥበቃን የሚያዝዝ ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ወዴት ነው? የሚል የለም፤
ትእዛዝህን አሰላሰልሁ፥ መንገድህንም እፈልጋለሁ።
እግዚአብሔር ለዘለዓለም ይነግሣል፤ ጽዮን ሆይ፥ አምላክሽ ለልጅ ልጅ ነው።
ምድር በሞላዋ የእግዚአብሔር ናት፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ።
አቤቱ፥ ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የተዘጋጀ ነው፥ አንተም መቼም መች እስከ ዘለዓለም ነህ።
በእርሱም አማካኝነት ወደቆምንበት ወደ ጸጋው በእምነት ተመራን፤ በእግዚአብሔርም ክብር ተስፋ እንመካለን።
እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።