ምድረ በዳውና ከተሞችዋ፥ የቄዳርም ነዋሪዎችና መንደሮች ድምፃቸውን ያንሡ፤ በዋሻም የሚኖሩ እልል ይበሉ፤ በተራሮችም ራስ ላይ ሆነው ይጩኹ።
መዝሙር 148:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተራሮችና ኮረብቶችም ሁሉ፥ የሚያፈራም ዛፍ ዝግባም ሁሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተራሮችና ኰረብቶች ሁሉ፣ የፍሬ ዛፎችና ዝግቦች ሁሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተራሮችና ኰረብቶች ሁሉ፥ የሚያፈራም ዛፍና ዝግባ ሁሉ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኰረብቶችና ተራራዎች፥ የፍሬ ተክሎችና የደን ዛፎች ሁሉ አመስግኑት። |
ምድረ በዳውና ከተሞችዋ፥ የቄዳርም ነዋሪዎችና መንደሮች ድምፃቸውን ያንሡ፤ በዋሻም የሚኖሩ እልል ይበሉ፤ በተራሮችም ራስ ላይ ሆነው ይጩኹ።
እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ምሕረትን አድርጎአልና ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ ይከበራልና የምድር መሠረቶች መለከትን ይንፉ፤ ተራሮችና ኮረብቶች በውስጣቸው ያሉ ዛፎች ሁሉ፥ እልል ይበሉ።
እግዚአብሔር ሕዝቡን ይቅር ብሎአልና፥ ከሕዝቡም ችግረኞቹን አጽንቶአልና። ሰማያት ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ምድርም ደስ ይበላት፤ ተራሮችም እልል ይበሉ።