ጐልማሶችና ደናግል፥ ሽማግሌዎችና ልጆች፤
ወጣት ወንዶችና ደናግል፣ አረጋውያንና ልጆች ያመስግኑት።
ጉልማሶችና ልጃገረዶች፥ ሽማግሌዎችና ልጆች፥
ጐልማሶችና ልጃገረዶች፥ ሽማግሌዎችና ልጆች ሁሉ አመስግኑት።
ከተማቸው በረሃ ትሁን፥ በድንኳኖቻቸውም የሚቀመጥ አይገኝ፤
ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፥ ስለ ጠላት፥ ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ።
በዚያን ጊዜም ደናግሉ በዘፈን ደስ ይላቸዋል፤ ጐበዛዝቱና ሽማግሌዎቹም በአንድ ላይ ደስ ይላቸዋል፤ እኔም ልቅሶአቸውን ወደ ደስታ እመልሳለሁ፤ ከኀዘናቸውም ደስ አሰኛቸዋለሁ።
በጎነቱ እንዴት ታላቅ ነው! ውበቱስ እንዴት ታላቅ ነው! እህል ጐበዛዝቱን፥ ጉሽ ጠጅም ቈነጃጅቱን ያለመልማል።
ወደ ደብረ ዘይት ዐቀበት መውረጃም በደረሱ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ በሙሉ ስለ አዩት ኀይል ሁሉ ደስ ይላቸውና እግዚአብሔርን በታላቅ ቃል ያመሰግኑት ዘንድ ጀመሩ።