የምድር ነገሥታት፥ አሕዛብም ሁሉ፥ አለቆች፥ የምድርም ፈራጆች ሁሉ፤
የምድር ነገሥታትና ሕዝቦች ሁሉ፣ መሳፍንትና የምድር ገዦች ሁሉ፣
የምድር ነገሥታትና አሕዛብ ሁሉ፥ አለቆችና የምድር ፈራጆች ሁሉ፥
ነገሥታትና የምድር ሕዝቦች፥ መሳፍንትና ፈራጆች ሁሉ አመስግኑት።
ሰውስ በዘመኑ እንደ ሣር ነው፤ እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል፤
ነገሥታትም አሳዳጊዎች አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፤ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።”
ነገሥታት በብርሃንሽ፥ አሕዛብም በፀዳልሽ ይሄዳሉ።
አሕዛብም በብርሃንዋ ይመላለሳሉ፤ የምድርም ነገሥታት ክብራቸውን ወደ እርስዋ ያመጣሉ፤