ለእጆቼ ጠብን፥ ለጣቶቼም ሰልፍን ያስተማራቸው አምላኬ እግዚአብሔር ይመስገን፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ልመናዬን አድምጥ፤ በታማኝነትህና በጽድቅህም፣ ሰምተህ መልስልኝ።
ልጁ ባሳደደው ጊዜ፥ የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ ልመናዬን አድምጥ፥ በታማኝነትህ፥ በጽድቅህም መልስልኝ።
እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ! ለምሕረት የማደርገውን ልመና አድምጥ! በታማኝነትህና በእውነተኛነትህ ለጸሎቴ መልስ ስጠኝ!
አቤቱ ሁሉን የምትገዛ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ አሁንም ለባሪያህና ለቤቱ የተናገርኸውን ለዘለዓለም አጽናው፤ አሁንም እንደ ተናገርህ አድርግ።
ኀያላኖቻቸው በዓለት አጠገብ ተጣሉ፥ ተችሎኛልና ቃሌን ስሙኝ።
አቤቱ፥ በኀይሌ እወድድሃለሁ።
ኀጢአታቸው የተተወላቸው፥ በደላቸውንም ሁሉ ያልቈጠረባቸው ብፁዓን ናቸው።
ሕዝብህን በጽድቅ፥ ድሆችህንም በፍርድ ይዳኝ ዘንድ።
በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።