ከሰወሩብኝ ወጥመድ፥ ዐመፃንም ከሚያደርጉ ሰዎች እንቅፋት ጠብቀኝ።
ዙሪያዬን የከበቡኝ ሰዎች ራስ፣ የከንፈራቸው መዘዝ ይጠምጠምበት።
አቤቱ፥ ከምኞቴ የተነሣ ለክፉዎች አትስጠኝ፥ ተንኮላቸው እንዲሳካ አትፍቀድ።
የከበቡኝ ጠላቶቼ በእኔ ላይ ያቀዱትን ሤራ በእነርሱ ላይ እንዲፈጸም አድርግ።
ከተአምራትህ የተነሣ አሕዛብ ይደንግጣሉ፥ በምድር ዳርቻም የሚኖሩ ይፈራሉ፤ በጥዋት ይወጣሉ፥ ማታም ይደሰታሉ።
ጉዳቱ በራሱ ይመለሳል፥ ዐመፃውም በአናቱ ላይ ትወርዳለች።
የሕይወት ምንጭ በጻድቃን አፍ ነው፥ የኃጥኣንን አፍ ግን ጥፋት ይከድነዋል።
የእግዚአብሔር በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ነው። የኃጥኣንን አፍ ግን ኀዘን በድንገት ይዘጋዋል።
ኀጢአተኛ ሰው በከንፈሩ ኀጢአት ወደ ወጥመድ ይወድቃል፤ ጻድቅ ግን ከእርሱ ያመልጣል። አስፍቶ የሚመለከት ሰው ብዙ ምሕረትን ያገኛል። ድንገት በበር የሚገናኝ ግን ነፍሳትን ያስጨንቃል።
የአላዋቂ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።
ሕዝቡም ሁሉ መልሰው “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን፤” አሉ።
ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፦ እጃችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አላደረገም እንዳይሉ፥ በቍጣ ጠላት ሆኑኝ።