መዝሙር 135:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድርን በውኃ ላይ ያጸና፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰማይና በምድር፣ በባሕርና በጥልቅ ሁሉ ውስጥ፣ እግዚአብሔር ደስ ያሠኘውን ሁሉ ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰማይና በምድር በባሕርና በጥልቆች ሁሉ፥ ጌታ የወደደውን ሁሉ አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰማይና በምድር፥ በጥልቅ ባሕሮችም የወደደውን ሁሉ ያደርጋል። |
በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እናገራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች፤ የመከርሁትንም ሁሉ አደርጋለሁ እላለሁ።
እነሆ ነጐድጓድን የሚያጸና፥ ነፋስንም የፈጠረ፥ የመሢሕን ነገር ለሰው የሚነግር፥ ንጋትን ጭጋግ የሚያደርግ፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ የሚረግጥ፥ ስሙ ሁሉን የሚችል ጌታ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።”
አዳራሹን በሰማይ የሠራ፥ ትእዛዙንም በምድር ላይ የመሠረተ፥ የባሕርንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት የሚያፈስሰው እርሱ ነው፤ ስሙም ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር ነው።