የኤርትራን ባሕር ፈጽሞ የከፈለ፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ ስምህ ዘላለማዊ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ መታሰቢያህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።
አቤቱ፥ ስምህ ለዘለዓለም ነው፥ ዝክርህም ለልጅ ልጅ ነው፥
እግዚአብሔር ሆይ! ስምህ ዘወትር ሲታወጅ ይኖራል፤ ትውልድ ሁሉ ያስታውሱሃል።
ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፥ እንዲሁ ኀጢአታችንን ከእኛ አራቀ።
አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራላቸዋል፤
ሠራዊቱ ሁሉ፥ ፈቃዱን የሚያደርጉ አገልጋዮቹ፥ እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል።
ፍጻሜአቸውን አውቅ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር መቅደስ እስክገባ ድረስ፥
አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ፥ ምስጋናህ በሰማዮች ላይ ከፍ ከፍ ብሎአልና።
አቤቱ፥ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ።
አቤቱ፥ አንተ ለልጅ ልጅ ሁሉ መጠጊያ ሆንህልን።
ዳግመኛም እግዚአብሔር ሙሴን አለው፥ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ፦ የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ላከኝ፤ ይህ ለዘለዓለም ስሜ ነው፤ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።
ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነኝ። በቤትአዎንም አገኘኝ፤ በዚያም ከእኔ ጋር ተነጋገረ።
ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።’
እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ!