Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 8:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አቤቱ ጌታ​ችን፥ ስምህ በም​ድር ሁሉ እጅግ ተመ​ሰ​ገነ፥ ምስ​ጋ​ናህ በሰ​ማ​ዮች ላይ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው! ክብርህ ከሰማያት በላይ፣ ከፍ ከፍ ብሏል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለመዘምራን አለቃ በዋሽንት፥ የዳዊት መዝሙር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ጌታችንና እግዚአብሔር ሆይ! ስምህ በዓለም ሁሉ የገነነ ነው። ክብርህንም ከሰማያት ሁሉ በላይ አድርገሃል።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 8:1
27 Referencias Cruzadas  

“በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰው ጋር በም​ድር ላይ ይኖ​ራ​ልን? እነሆ ሰማይ ከሰ​ማ​ያ​ትም በላይ ያለው ሰማይ ይይ​ዝህ ዘንድ አይ​ች​ልም፤ ይል​ቁ​ንስ እኔ ለስ​ምህ የሠ​ራ​ሁት ቤት እን​ዴት ያንስ!


ነፍሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ያመ​ሰ​ግ​ናሉ። ስሙ ብቻ​ውን ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፥ በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።


መን​ገ​ድ​ህን ለአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግለጥ፥ በእ​ር​ሱም ታመን፥ እር​ሱም ያደ​ር​ግ​ል​ሃል።


ዐዋቂ ሲደ​ግ​ም​ባት የአ​ስ​ማ​ተ​ኛ​ውን ቃል እን​ደ​ማ​ት​ሰማ።


አቤቱ፥ ወደ አንተ የለ​መ​ን​ሁ​ትን ጸሎ​ቴን ስማኝ፥ ከጠ​ላ​ትም ጥር​ጥር ነፍ​ሴን አድ​ናት።


በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉኝ ከራሴ ጠጉር በዙ፤ በዐ​መፅ የሚ​ከ​ብ​ቡኝ ጠላ​ቶቼ በረቱ፤ ያል​ወ​ሰ​ድ​ሁ​ትን ይከ​ፈ​ሉ​ኛል።


አቤቱ፥ ጌታ​ችን፥ ስምህ በም​ድር ሁሉ እጅግ ተመ​ሰ​ገነ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ማ​ል​ክት ማኅ​በር ቆመ፥ በአ​ማ​ል​ክ​ትም መካ​ከል ይፈ​ር​ዳል።


አቤቱ፦ ምድ​ር​ህን ይቅር አልኽ። የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ምርኮ መለ​ስህ።


አቤቱ፦ በአ​ማ​ል​ክት መካ​ከል አን​ተን የሚ​መ​ስል ማን ነው? በቅ​ዱ​ሳ​ንም ዘንድ እንደ አንተ የከ​በረ ማን ነው? በም​ስ​ጋና የተ​ደ​ነ​ቅህ ነህ፤ ድን​ቅ​ንም የም​ታ​ደ​ርግ ነህ፤


ጕሮ​ሮው እጅግ ጣፋጭ ነው፥ ሁለ​ን​ተ​ና​ውም የተ​ወ​ደደ ነው፤ እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ ልጅ ወን​ድሜ ይህ ነው፥ ወዳ​ጄም ይህ ነው።


አቤቱ፥ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ አንተ ግዛን፤ ከአ​ንተ በቀር ሌላ አና​ው​ቅ​ምና፤ ስም​ህ​ንም እን​ጠ​ራ​ለን።


እግዚአብሔር ከቴማን፥ ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል። ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል።


ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው፥ እንዴት ልጁ ይሆናል?” አላቸው።


ቶማ​ስም፥ “ጌታዬ አም​ላ​ኬም” ብሎ መለሰ።


የወ​ረ​ደው እርሱ ነው፤ ሁሉ​ንም ይመላ ዘንድ ከሰ​ማ​ያት ሁሉ በላይ የወ​ጣው ደግሞ እርሱ ነው።


“በዚህ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፉ​ትን የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ታደ​ርግ ዘንድ፥ ይህ​ንም ክቡ​ርና ምስ​ጉን ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክ​ህን ትፈራ ዘንድ ባት​ሰማ፥


ክር​ስ​ቶ​ስን አገ​ለ​ግ​ለው ዘንድ፥ ሁሉን የተ​ው​ሁ​ለት፥ እንደ ጕድ​ፍም ያደ​ረ​ግ​ሁ​ለት የጌ​ታ​ዬን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ኀይ​ልና ገና​ና​ነት ስለ​ማ​ውቅ ሁሉን እንደ ኢም​ንት ቈጠ​ር​ሁት።


ቅዱ​ስና ያለ ተን​ኰል፥ ነው​ርም የሌ​ለ​በት፥ ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ችም የተ​ለየ፥ ከሰ​ማ​ያ​ትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ ሊቀ ካህ​ናት ይገ​ባ​ናል።


እንደ ብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ እንደ ብዙ ውሃዎችም ድምፅ፥ እንደ ብርቱም ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos