ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።
መዝሙር 131:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔር እንደ ማለ፥ ለያዕቆብም አምላክ እንደ ተሳለ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ነፍሴን ጸጥ፣ ዝም አሠኘኋት፤ ጡት የጣለ ልጅ ዐርፎ እናቱ ላይ እንደሚቀመጥ፣ ነፍሴ ጡት እንዳስተዉት ሕፃን በውስጤ ጸጥ አለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሴን አሳረፍኋት፥ የእናቱንም ጡት እንዳስተዉት ሕጻን ዝም አሰኘኋት፥ ነፍሴ የእናቱን ጡት እንዳስተዉት በእኔ ውስጥ ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ጡት የተወ ሕፃን በእናቱ ደረት ላይ እንደሚለጠፍ እኔም ዝምተኛና ጸጥተኛ ሆንኩ። |
ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።
አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ እንጨትና ውኃ በሌለበት ምድረ በዳ ሥጋዬን ለአንተ እንዴት ልዘርጋልህ
የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “ብትጸጸትና ብታለቅስ ትድናለህ፤ የት እንዳለህም ታውቃለህ፤ በከንቱ ታምነሃልና፤ ኀይላችሁም ከንቱ ይሆናል፤ እናንተ ግን መስማትን እንቢ አላችሁ፤
ወንድሞቻችን ሆይ፥ በአእምሮ እንደ ሕፃናት አትሁኑ፤ ነገር ግን ለክፉ ነገር እንደ ሕፃናት ሁኑ፤ በዕውቀትም ፍጹማን ሁኑ።
ስለ ወንዶችና ስለ ሴቶች ልጆቻቸውም የሕዝቡ ሁሉ ልብ አዝኖ ነበርና ሕዝቡ ሊወግሩት ስለ ተናገሩ ዳዊት እጅግ ተጨነቀ፤ ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ራሱን አጽናና።