መዝሙር 130:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ራሴን አዋረድሁ እንጂ። ለነፍሴ ዋጋዋን ትሰጣት ዘንድ፤ የእናቱንም ጡት እንዳስጣሉት በቃሌ ጮኽሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ ሆይ፤ ድምፄን ስማ፤ ጆሮዎችህ የልመናዬን ቃል፣ የሚያዳምጡ ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ድምፄን ስማ፥ ጆሮህ የልመናዬን ቃል ያድምጥ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ልመናዬን ስማ! ምሕረትህን ፈልጌ ስጮኽም አድምጠኝ! |
ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባሪያህን ጸሎት፥ ስምህንም ይፈሩ ዘንድ የሚወድዱትን የባሪያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬም ለባሪያህ አከናውንለት፤ በዚህም ሰው ፊት ምሕረትን ስጠው።” እኔም ለንጉሡ ጠጅ አሳላፊ ነበርሁ።
እኔ ባሪያህ ዛሬ በፊትህ ስለ ባሪያዎችህ ስለ እስራኤል ልጆች ሌሊትና ቀን የምጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮዎችህ ያድምጡ፤ ዐይኖችህም ይከፈቱ፤ በአንተ ላይም ያደረግነውን የእስራኤልን ልጆች ኀጢአት ለአንተ እንናዘዛለን፤ እኔም፥ የአባቴም ቤት በድለናል።
አቤቱ፥ ጆሮህን አዘንብልና ስማ፤ አቤቱ፥ ዐይንህን ክፈትና በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ የላከውን የሰናክሬምን ቃል ተመልከት።