ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፥ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና፤ እግዚአብሔርን መፍራት በዐይናቸው ፊት የለም።
ቸርነቱ ታምኛለሁና፣ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ።
እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ፥ ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል። ለረዳኝን ጌታ እዘምራለሁ፥ መልካምን አድርጎልኛልና።
እግዚአብሔር ሆይ! በጎ ነገር ስላደረግህልኝ ለአንተ እዘምራለሁ።
እኔ ሰላማዊ ስሆን በተናገርኋቸው ጊዜ በከንቱ ይጠሉኛል።
ለመንጠቅ እንደሚያሸምቅ አንበሳ በላዬ አፋቸውን ከፈቱ።
የእግዚአብሔር ቃል የእሳቱን ነበልባል ይቈርጣል።
አሕዛብ በሠሩት በደላቸው ጠፉ፥ በዚያችም በሸሸጓት ወጥመድ እግራቸው ተጠመደ።