ከማለዳው ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊት ነፍሴ በእግዚአብሔር ታመነች። ከማለዳ ጀምሮ እስራኤል በእግዚአብሔር ታመነ።
ገና ከመብቀሉ እንደሚደርቅ፣ በጣራ ላይ እንደ በቀለ ሣር ይሁኑ፤
በሰገነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፥ ሳይነቀል እንደሚደርቅ፥
በቤት ጣራ ላይ እንደሚበቅልና ከማደጉ በፊት እንደሚደርቅ ሣር ይሁን።
ከእነርሱም በኋላ እነሆ የሰለቱና በነፋስ የተመቱ ሌሎች ሰባት እሸቶች ወጡ፤
ስለዚህም የሚኖሩባቸው ሰዎች እጆቻቸው ዝለዋል፤ ደንግጠውም አፍረዋል፤ እንደ ምድረ በዳ ሣር፥ እንደ ለምለምም ቡቃያ፥ በሰገነትም ላይ እንዳለ ሣር፥ ሳይሸት ዋግ እንደ መታውም እህል ሆነዋል።
ፍላጾችህ ወግተውኛልና፥ እጅህንም በእኔ ላይ አክብደህብኛልና።
እጃቸውንም አዝላለሁ፤ ይደርቃሉም፤ በሰገነት ላይ እንዳለ ደረቅ ሣርም ሳያሸት ዋግ እንደ መታው እህልም ይሆናሉ።
ፀሐይ በወጣ ጊዜ ግን ጠወለገ፥ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ።